እግዚአብሔርም ነቢዩን እንዲህ አለው፤ “ከይሁዳ ሀገር ወደ ሬማት ወደ ሞዓቡ ሹም ወደ መቃቢስ ተመለስ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል በለው፦ በኀይሌ ጽናትና በሠራዊቴ ቅድስቲቱን ከተማ አጠፋኋት እንዳትል ከተማዬን ታጠፋ ዘንድ የአንተ ፈጣሪ እኔ እግዚአብሔር በፈቃዴ ላክሁህ እንጂ ይህን ነገር ያደረግኸው አንተ አይደለህም፤