ያንጊዜም በመከራ የሚያሠቃዩአቸው አሕዛብን ያስነሣባቸው ነበር፤ በአሠቃዩአቸውና ባሳዘኑአቸውም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጮሁ ነበር፤ የዚያን ጊዜም ራርቶ ይቅር ይላቸው ነበር። የእጁ ፍጥረት ስለ ሆኑ ይወድዳቸው ነበርና።