የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮ​ራም ከሰ​ማ​ርያ ወጥቶ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ በዚያ ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ከሰማርያ ተነሥቶ በመሄድ እስራኤልን ሁሉ አሰባሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ወዲያውኑ ከሰማርያ ወጥቶ ወታደሮቹን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ወዲያውኑ ከሰማርያ ወጥቶ ወታደሮቹን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮራም ከሰማርያ ወጥቶ እስራኤልን ሁሉ አሰለፈ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 3:6
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አክ​ዓ​ብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ደነ​ገጠ፤ ልብ​ሱ​ንም ቀደደ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰም ሄደ፤ በሰ​ው​ነ​ቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡ​ቴ​ንም በገ​ደ​ለ​በት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።


አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ የሞ​ዓብ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ከዳው።


ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ።


በባማ ባለው በቤ​ዜ​ቅም ቈጠ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።


ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን ጠርቶ በጌ​ል​ጌላ ቈጠ​ራ​ቸው፤ አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች፥ ከይ​ሁ​ዳም ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበሩ።