የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ በለ​መ​ለ​መ​ውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በኰረብታ ላይ ባሉ ማምለኪያ ስፍራዎችና በተራሮች ዐናት ላይ፣ በየዛፉም ጥላ ሥር መሥዋዕት አቀረበ፤ ዕጣንም ዐጠነ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አካዝ በየኰረብቶች ላይ በተሠሩት የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና በእያንዳንዱም ዛፍ ሥር መሥዋዕት በማቅረብ ዕጣን አጠነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አካዝ በየኰረብቶች ላይ በተሠሩት የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና በእያንዳንዱም ዛፍ ሥር መሥዋዕት በማቅረብ ዕጣን አጠነ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመስገጃዎችና በኮረብቶቹ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠዋና ያጥን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 16:4
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠ​ሉም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ች​ንም ለራ​ሳ​ቸው አቆሙ።


ኢዮ​አ​ስም ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ገ​ባ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍ​ሱም ዋጋ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ገን​ዘብ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ፈቃድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡ​ትን ገን​ዘብ ሁሉና፥


ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ።


“በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ሩና የሚ​ያ​ነጹ፥ በም​ግብ ቦታም የእ​ሪ​ያን ሥጋ፥ አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ር​ንም አይ​ጥ​ንም የሚ​በሉ በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ከለ​መ​ለሙ ዛፎች በታ​ችና በረ​ዘ​ሙት ኮረ​ብ​ቶች ላይ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንና የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዳ​ቸ​ውን ያስ​ባሉ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ቀ​መ​ጥ​በት የዙ​ፋኔ ስፍ​ራና የእ​ግሬ ጫማ መረ​ገጫ ይህ ነው። ዳግ​መ​ኛም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውና በከ​ፍ​ታ​ዎ​ቻ​ቸው በአ​ለው በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያ​ረ​ክ​ሱም።


ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸው በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ በወ​ደቁ ጊዜ በረ​ዣ​ዥም ኮረ​ብታ ሁሉ፥ በተ​ራ​ሮ​ችም ራሶች ሁሉ፥ በዕ​ን​ጨ​ቱም ጥላ ሥር ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ፥ መል​ካም መዓ​ዛን ባጠ​ኑ​በት ከቅ​ጠሉ ሁሉ በታች ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸው በወ​ደቁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


እና​ንተ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አ​ቸው አሕ​ዛብ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ለ​ኩ​ባ​ቸ​ውን፥ በረ​ዥም ተራ​ሮች፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ከለ​ም​ለ​ምም ዛፍ በታች ያለ​ውን ስፍራ ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ አጥ​ፉት፤