ከዚህ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቻቸው ካህናቱና፥ ሌዋውያኑም፥ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትም ሁሉ ቤተ መቅደስን ይሠሩ ዘንድ ጀመሩ።