የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብላ​ቴ​ናው ደግሞ ለሳ​ኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እር​ሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድም ይነ​ግ​ረ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዩ፣ “እኔ የአንድ ሰቅል ጥሬ ብር ሩብ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ዘንድ ገንዘቡን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አገልጋዩ፦ “እነሆ፥ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ ለሳኦል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አገልጋዩም “እነሆ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለችኝ፤ እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል ይነግረናል” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፦ እነሆ፥ በእጄ የሰቅል ብር ሩቡ አለኝ፥ እርሱንም መንገዳችንን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጣለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 9:8
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ ምሳም ብላ፥ ስጦ​ታም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


በእ​ጅ​ሽም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዐሥር እን​ጀ​ራና የወ​ይን እሸት አን​ድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በል​ጁም የሚ​ሆ​ነ​ውን ይነ​ግ​ር​ሻል” አላት።


ብላ​ቴ​ና​ውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በዚ​ህች ከተማ አለ፤ እር​ሱም የተ​ከ​በረ ሰው ነው፤ የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጸ​ማል፤ አሁ​ንም ወደ​ዚያ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገድ ይነ​ግ​ረ​ና​ልና” አለው።