Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አገልጋዩም “እነሆ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለችኝ፤ እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል ይነግረናል” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አገልጋዩ፣ “እኔ የአንድ ሰቅል ጥሬ ብር ሩብ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ዘንድ ገንዘቡን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አገልጋዩ፦ “እነሆ፥ እኔ የአንድ ጥሬ ብር አንድ አራተኛው እጅ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ ለሳኦል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ብላ​ቴ​ናው ደግሞ ለሳ​ኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እር​ሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድም ይነ​ግ​ረ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፦ እነሆ፥ በእጄ የሰቅል ብር ሩቡ አለኝ፥ እርሱንም መንገዳችንን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጣለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:8
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩን “ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ” አለው።


ዐሥር እንጀራ፥ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር. ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል።”


አገልጋዩም “ቈይ! እስቲ በዚህች ከተማ በጣም የተከበረ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱ የሚናገረው ቃል ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ ስለዚህም ወደ እርሱ እንሂድ፤ ምናልባትም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል እርሱ ሊነግረን ይችል ይሆናል” ሲል መለሰለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች