የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከመ​ጮኽ ዝም አት​በል። እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ነ​ናል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳሙኤልንም፣ “አምላካችን እግዚአብሔር ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ስለ እኛ ወደ እርሱ መጸለይህን አታቋርጥ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳሙኤልንም፥ “አምላካችን ጌታ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ስለ እኛ ወደ እርሱ መጸለይህን አታቋርጥ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳሙኤልንም፦ “ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጸለይን አታቋርጥ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች ሳሙኤልን፦ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ትጸልይልን ዘንድ አትታክት አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 7:8
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።


ጽድቄ እንደ ብር​ሃን፥ ማዳ​ኔም እን​ደ​ሚ​በራ ፋና እስ​ኪ​ወጣ ድረስ ስለ ጽዮን ዝም አል​ልም፤ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጸጥ አል​ልም።


እነ​ርሱ ግን ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የቀ​ሩት ዕቃ​ዎች ወደ ባቢ​ሎን እን​ዳ​ይ​ሄዱ ወደ ሠራ​ዊት ጌታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ለሉ።”


እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።