የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም ወስ​ዳ​ችሁ አን​ዲት አዲስ ሰረ​ገላ ሥሩ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡም፥ ቀን​በር ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ቸ​ውን ሁለት ላሞች በሰ​ረ​ገላ ጥመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለይ​ታ​ችሁ ወደ ቤት መል​ሱ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም ወስዳችሁ አንዲት ሰረገላ ሥሩ፥ የሚያጠቡም፥ ቀን በር ያልተጫነባቸውን ሁለት ላሞች በሰረገላ ጥመዱአቸው፥ እንቦሶቻቸውንም ለይታችሁ ወደ ቤት መልሱአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 6:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት በተ​ገኘ በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ አኖ​ሩ​አት። ዖዛና ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰረ​ገ​ላ​ውን ይነዱ ነበር።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው የሕጉ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ መል​ካ​ሚ​ቱን፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ቀይ ጊደር ያመ​ጡ​ልህ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው።


ለተ​ገ​ደ​ለ​ውም ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነች የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከላ​ሞች ለሥራ ያል​ደ​ረ​ሰ​ች​ውን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ጊደር ይው​ሰዱ፤


የዚ​ያ​ችም ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጊደ​ሪ​ቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳ​ለ​በት ወዳ​ል​ታ​ረ​ሰና ዘርም ወዳ​ል​ተ​ዘ​ራ​በት ሽለቆ ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያም በሸ​ለ​ቆው ውስጥ የጊ​ደ​ሪ​ቱን ቋን​ጃ​ዋን ይቈ​ር​ጣሉ።