Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወስ​ዳ​ችሁ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ አኑ​ሩ​አት፤ ስለ​በ​ደል መባእ ካሳ አድ​ር​ጋ​ችሁ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ትን የወ​ር​ቁ​ንም ዕቃ በሣ​ጥን ውስጥ አድ​ር​ጋ​ችሁ በታ​ቦቷ አጠ​ገብ አኑ​ሩት፤ ትሄ​ድም ዘንድ ስደ​ዱ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ በታቦቱም አጠገብ ባለው ሣጥን ውስጥ ለበደል መሥዋዕት የምትልኩትን የወርቅ ምስሎች አስቀምጡ፤ በፈለገውም መንገድ እንዲሄድ ልቀቁት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የጌታን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን ልዩ ልዩ የወርቅ ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፤ መንገዱንም እንዲሄድ ልቀቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደላችሁም እንዲከፈል ከእርሱ ጋር ለመላክ የሠራችሁትን ልዩ ልዩ ወርቅ በሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ በታቦቱ ጐን አስቀምጡ፤ ሠረገላውንም መንገድ አስይዛችሁ እንዲንቀሳቀስ ተዉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሩት፥ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን የወርቁን ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፥ ይሄድም ዘንድ ስደዱት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 6:8
2 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች