በነጋም ጊዜ መንፈሱ ታወከችበት፤ የግብፅ ሕልም ተርጓሚዎችንና ጠቢባንን ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን ሕልሙን የሚተረጕምለት አልተገኘም።
1 ሳሙኤል 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠንቋዮችንም ጠርተው፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራዋስ በምን እንስደዳት? አስታውቁን” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ካህናታቸውንና አስማተኞቻቸውን ጠርተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁአቸው፤ “ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ምን ማድረግ የሚሻለን ይመስላችኋል? ወደ ስፍራው እንዲመለስ ብናደርግ በምን ሁኔታ እንላከው? ዘዴውን ንገሩን” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠርተው፥ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራውስ በምን እንስደደው? አስታውቁን አሉ። |
በነጋም ጊዜ መንፈሱ ታወከችበት፤ የግብፅ ሕልም ተርጓሚዎችንና ጠቢባንን ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን ሕልሙን የሚተረጕምለት አልተገኘም።
ሕዝቡን የያዕቆብን ቤት ትቶአልና፤ ምድራቸው እንደ ቀድሞው እንደ ፍልስጥኤማውያን ምድር በሟርት ተሞልቶአልና፤ እንደ ባዕድ ልጆችም ሆነዋልና፤ ብዙ እንግዶች ልጆችም ተወልደውላቸዋልና።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፥ “በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎችም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእስራኤል አምላክ ታቦትም ወደ ጌት ሄደች።