ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
1 ሳሙኤል 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ታቦት ወደዚያ በገባች ጊዜ በከተማው ሁሉ ታላቅ ሁከት ሆኖአልና። በሕይወትም ያሉ፥ ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፤ የከተማዪቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያልሞቱትን ደግሞ ዕባጩ ያሠቃያቸው ስለ ነበር፣ የከተማዪቱ ጩኸት እስከ ሰማይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያልሞቱትን ደግሞ ዕባጩ ያሠቃያቸው ስለ ነበር፥ የከተማዪቱ ጩኸት እስከ ሰማይ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሞት የተረፉትም የእባጩ በሽታ በርትቶባቸው ስለ ነበር ሕዝቡ ርዳታ ለማግኘት ወደ አማልክታቸው በማልቀስ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፥ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ። |
ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
ፈርዖንም፥ ሹሞቹም ሁሉ፥ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ።
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።
ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ይሆናል።
እንዲህም አለው፥ “ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም ሀገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ልቅሶአቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕዝቤን ሥቃያቸውን ተመልክችአለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል።”