Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ሁሉ ሰብ​ስ​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ስደ​ዱ​አት፤ እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን እን​ዳ​ት​ገ​ድል በስ​ፍ​ራዋ ትቀ​መጥ” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ አለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደገና ወደ ፍልስጥኤማውያን ነገሥታት ሁሉ መልእክተኞች ልከው “እኛንና ቤተሰባችንን ሁሉ ከመፍጀቱ በፊት የእስራኤልን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ስፍራው መልሳችሁ ላኩ” አሉ፤ እግዚአብሔር በብርቱ ስለ ቀጣቸው በመላ ከተማይቱ የሚያስጨንቅ የሞት ፍርሀት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 5:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እን​ቅ​ፋት ይሆ​ን​ብ​ናል? አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ል​ኩት ዘንድ ሰዎ​ችን ልቀቅ፤ ግብ​ፅስ እንደ ጠፋች ገና አታ​ው​ቅ​ምን?” አሉት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ።


እጁ ከእ​ና​ን​ተና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ከም​ድ​ራ​ች​ሁም ይቀ​ልል ዘንድ፥ የእ​ባ​ጫ​ች​ሁን ምሳሌ፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን የአ​ይ​ጦ​ችን ምሳሌ አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብ​ርን ስጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች