የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፣ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፥ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከማረኩ በኋላ ከአቤንዔዜር አሽዶድ ተብላ ወደምትጠራ ከተማቸው ወሰዱአት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ይዘውት መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 5:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​ሦር ንጉሥ አርና ጣን​ታ​ንን በሰ​ደደ ጊዜ፥ እር​ሱም ወደ አዛ​ጦን በመጣ ጊዜ፥ አዛ​ጦ​ን​ንም ወግቶ በያ​ዛት ጊዜ፥


በፋ​ርስ ሀገ​ሮ​ችና በግ​ብፅ ሀገ​ሮች ዐው​ጁና፥ “በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በው​ስ​ጥ​ዋም የሆ​ነ​ውን ታላ​ቁን ተአ​ምር፥ በመ​ካ​ካ​ል​ዋም ያለ​ውን ግፍ ተመ​ል​ከቱ” በሉ።


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።


በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለጦ​ር​ነት በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ወጡ፤ በአ​ቤ​ኔ​ዜር አጠ​ገ​ብም ሰፈሩ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ፌቅ ሰፈሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ረ​ከች፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞቱ።


እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ተማ​ር​ካ​ለ​ችና ክብር ከእ​ስ​ራ​ኤል ለቀቀ” አሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሰባት ወር ተቀ​መ​ጠች። ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።