የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ፣ ምድሪቱ እስክትናወጥ ድረስ እስራኤላውያን ሁሉ ታላቅ የደስታ ጩኸት አሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታ የኪዳኑ ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ፥ ምድር እስክትናወጥ ድረስ እስራኤላውያን ሁሉ ታላቅ የሆታ ድምፅ አሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቃል ኪዳኑም ታቦት በዚያ ቦታ በደረሰ ጊዜ እስራኤላውያን ምድር እስክትናወጥ ድረስ ታላቅ የእልልታና የሆታ ድምፅ አሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 4:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶ​ቅና ከእ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ፈጽሞ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ አብ​ያ​ታር ወጣ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ይህ ነው እያ​ላ​ችሁ በሐ​ሰት ቃል በራ​ሳ​ችሁ አት​ታ​መኑ።


ክፉ ቀንን ለሚ​ፈ​ል​ጓት፥ የሐ​ሰት ሰን​በ​ታ​ትን ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ር​ቡና አንድ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


ሕዝ​ቡም ጮኹ፥ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፉ፤ ሕዝ​ቡም የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥ​ሩም ወደቀ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታ​ቸው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ሮጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም እጅ አደ​ረጉ።


ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።”


የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ል​ል​ታ​ውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእ​ል​ልታ ድምፅ ምን​ድን ነው?” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረ​ሰች አስ​ተ​ዋሉ።