Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሕዝ​ቡም ጮኹ፥ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፉ፤ ሕዝ​ቡም የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥ​ሩም ወደቀ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታ​ቸው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ሮጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም እጅ አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ፤ የመለከቱ ድምፅ ተሰምቶ፣ ሕዝቡ በኀይል ሲጮኽ ቅጥሩ ፈረሰ፤ እያንዳንዱም ሰው ሰተት ብሎ ገባ፤ ከተማዪቱም በእጃቸው ወደቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ በቀጥታ አቅንቶ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ያዝዋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ እምቢልታ ተነፋ፤ ሕዝቡም የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ አሰሙ የከተማይቱም ቅጽሮች ፈረሱ፤ ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ኮረብታውን ወጥቶ ሰተት ብሎ ወደ ከተማይቱ በመግባት በቊጥጥሩ ሥር አደረጋት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፥ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ወሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 6:20
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ብ​ያና በሕ​ዝቡ ፊት መታ​ቸው።


በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።


ሰባት ቀን ከዞ​ሩ​አት በኋላ የኢ​ያ​ሪኮ ቅጽር በእ​ም​ነት ወደቀ።


ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች