በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰፈር ከሳኦል ወገን አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።
1 ሳሙኤል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን አንድ የብንያም ሰው ከሰልፍ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ፤ ልብሱም ተቀድዶ ነበር፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት አንድ ብንያማዊ ልብሱን ቀዶ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፣ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ የብንያም ወገን የሆነ ሰው ልብሱን ቀዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፥ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገዱ ከብንያም ወገን የሆነ አንድ ሰው ከጦር ሜዳ ተነሥቶ በመገሥገሥ በዚያኑ ዕለት ሴሎ ደረሰ፤ ሐዘኑንም ለማሳወቅ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን አንድ የብንያም ሰው ከሰልፍ እየበረረ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ወደ ሴሎ መጣ። |
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰፈር ከሳኦል ወገን አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።
ትዕማርም አመድ ወስዳ በራስዋ ላይ ነሰነሰች፤ በላይዋ የነበረውንም ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ቀደደችው፤ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች።
ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብሱን ቀደደ፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።
ከሩቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላወቁትም፤ በታላቅ ድምፅም ጮኸው አለቀሱ፤ መጐናጸፊያቸውንም ቀደዱ፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።