የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤል ግን ከዚህ በፊት ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቀም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ገና አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያም ጊዜ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ጊዜ ሳሙኤል ጌታን ገና አላወቀም ነበር፤ የጌታም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳሙኤልም ከዚያ በፊት እግዚአብሔር ተናግሮት ስለማያውቅ የእግዚአብሔር ድምፅ መሆኑን አላወቀም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ አልጠራሁህም፥ ተመልሰህ ተኛ ብሎ መለሰ። ሳሙኤል ግን ገና እግዚአብሔርን አላወቀም ነበረ፥ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 3:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በውኑ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አል​ተ​ቀ​በ​ል​ንም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳለ ስንኳ አል​ሰ​ማ​ንም” አሉት።


እኔ ልጅ በነ​በ​ርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እና​ገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመ​ክር ነበር፤ በአ​ደ​ግሁ ጊዜ ግን የል​ጅ​ነ​ትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፥ “ሳሙ​ኤል! ሳሙ​ኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ዳግ​መኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። እር​ሱም፥ “አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም ተመ​ል​ሰህ ተኛ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ ጠራው። እር​ሱም ተነ​ሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን እንደ ጠራው አስ​ተ​ዋለ።