የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም በሉት፤ ‘ዕድሜህ ይርዘም! ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተ ሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም በሉት፤ ‘ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በደኅንነት ኑር፥ ለአንተና ለቤትህም ለአንተም ላሉት ሁሉ ሰላም ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 25:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ አት​ፍሩ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ የተ​ሰ​ወረ ገን​ዘብ ሰጣ​ችሁ፤ ብራ​ች​ሁ​ንስ መዝኜ ተቀ​ብ​ያ​ለሁ።”


አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ወደ ገባ​ች​ሁ​በት ቤትም አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ።


“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።


የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።


ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።


ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤