እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም።
1 ሳሙኤል 25:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ክፉ እንዳላደርግብሽ የከለከለኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባልመጣሽ ኖሮ፥ እስኪነጋ ድረስ ለናባል አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ባልቀረውም ብዬ ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕዳት እንዳላደርስብሽ የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! እንዲህ በቶሎ መጥተሽ ባታገኚኝ ኖሮ፣ እስኪነጋ ድረስ ለናባል አንድ ወንድ እንኳ ባልተረፈ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉዳት እንዳላደርስብሽ የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው ጌታን! እንዲህ በቶሎ መጥተሽ ባታገኚኝ ኖሮ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ለናባል አንድ ወንድ እንኳ ባልተረፈ ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንቺ ላይ ጒዳት ከማድረስ እግዚአብሔር ጠብቆኛል፤ ፈጥነሽ ወደ እኔ ባትመጪ ኖሮ ግን፥ ከናባል ወንዶች አንድ እንኳ ሳላስተርፍ ከንጋት በፊት ሁሉንም ለመግደል በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ክፉ እንዳላደርግብሽ የከለከለኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባልመጣሽ ኖሮ፥ እስኪነጋ ድረስ ለናባል አንድ ወንድ ስንኳ ባልቀረውም ነበር። |
እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም።
የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፥ “ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው ሀገር የሚኖሩ የአሞሬዎናውያን ነገሥት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድነንም፤ ርዳንም፤” አሉት።
በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፤ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፤ ከውስጣቸውም ሁለት በአንድ ላይ ሆነው አልተገኙም።
አቤግያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት አቁማዳ የወይን ጠጅ፥ አምስት የተዘጋጁ በጎች፥ አምስትም መስፈሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበለስ ጥፍጥፍ ወሰደች፥ በአህዮችም ላይ አስጫነች።
ለናባልም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ብንተው፥ እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ፤ እንዲህም ይጨምር” ብሎ ነበር።
አሁንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እንዳትገባና፥ እጅህን እንድታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።
ዳዊትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከናባል እጅ የስድቤን ፍርድ የፈረደልኝ፥ ባሪያውንም ከክፉዎች እጅ የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እግዚአብሔርም የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊትም ያገባት ዘንድ አቤግያን እንዲያነጋግሩለት ላከ።