Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀብሎ፣ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፤ ቃልሽን ሰምቻለሁ፤ የጠየቅሽኝንም ተቀብያአለሁ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀብሎ፥ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፤ ቃልሽን ሰምቻለሁ፤ የጠየቅሽኝንም ተቀብያአለሁ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ከዚያም በኋላ ዳዊት ያመጣችለትን ስጦታ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ተመልሰሽ ሂጂ፤ ልመናሽን ሰምቼአለሁ፤ የጠየቅሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፦ በደኅና ወደ ቤትሽ ሂጂ፥ እነሆ፥ ቃልሽን ሰማሁ፥ ፊትሽንም አከበርሁ አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:35
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም አለው፥ “ስለ እር​ስዋ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝን ያችን ከተማ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ኸው ልመ​ና​ህን ተቀ​ብ​ዬ​ሃ​ለሁ፤


ንጉ​ሡም፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኬብ​ሮን ሄደ።


ኤል​ሳ​ዕም ንዕ​ማ​ንን፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው። ጥቂት መን​ገ​ድም ከእ​ርሱ ራቀ።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”


እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እም​ነ​ትሽ አዳ​ነ​ችሽ፤ በሰ​ላም ሂጂ” አላት።


ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች