የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ ማለ​ደው፤ ዳዊ​ትም በአ​ንባ ውስጥ በነ​በ​ረ​በት ወራት ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከ ቈየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከቆየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህም ዐይነት ወላጆቹን በሞአብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው፤ እነርሱም ዳዊት እየተደበቀ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በዚያው ቈዩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሞዓብም ንጉሥ ፊት አመጣቸው፥ ዳዊትም በአምባ ውስጥ በነበረበት ወራት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 22:4
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ማልዶ በተ​ነሣ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።


በዚ​ያም ጊዜ ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በቤተ ልሔም ነበረ።


ዳዊ​ትም ወደ ነበ​ረ​ባት ወደ አን​ባ​ዪቱ ከብ​ን​ያ​ምና ከይ​ሁዳ ወገን ሰዎች ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት መጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለነ​ቢዩ ለጋድ እን​ዲህ አለው፦


የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


እኔም፥ “እንደ እኔ ያለ ሰው የሸ​ሸና፥ ነፍ​ሱ​ንስ ያድን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ የገባ ማን ነው? እኔስ አል​ገ​ባም” አል​ሁት።


አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።


ዳዊ​ትም ከዚያ በሞ​ዓብ ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ኝን እስ​ካ​ውቅ ድረስ አባ​ቴና እናቴ ከአ​ንተ ጋር ይቀ​መጡ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ነቢዩ ጋድም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአ​ን​ባው ውስጥ አት​ቀ​መጥ” አለው፤ ዳዊ​ትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተ​ማም መጥቶ ተቀ​መጠ፤