Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 22:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከ ቈየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከቆየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚህም ዐይነት ወላጆቹን በሞአብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው፤ እነርሱም ዳዊት እየተደበቀ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በዚያው ቈዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ ማለ​ደው፤ ዳዊ​ትም በአ​ንባ ውስጥ በነ​በ​ረ​በት ወራት ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በሞዓብም ንጉሥ ፊት አመጣቸው፥ ዳዊትም በአምባ ውስጥ በነበረበት ወራት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 22:4
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በማግስቱም ጧት ዳዊት ከመነሣቱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል የዳዊት ባለራእይ ወደ ሆነው ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ መጣ፤


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።


በዚያ ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሰራዊት በቤተ ልሔም ነበረ፤


ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።


እግዚአብሔርም የዳዊት ባለራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤


በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነቢዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ፣ በባለራእዩ በጋድ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል።


ንጉሥ ሕዝቅያስም በዳዊት፣ በንጉሡ ባለራእይ በጋድና በነቢዩ በናታን በተሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያኑን ጸናጽል፣ በገናና መሰንቆ አስይዞ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መደባቸው፤ ይህም በነቢያት አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።


እኔ ግን፣ “እንደ እኔ ያለ ሰው ሸሽቶ ይደበቃል? ወይም ደግሞ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ይገባዋልን? አልሄድም!” አልሁ።


በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ” ለምን ትሏታላችሁ?


በአንድ ስፍራ ሲያሳድዷችሁ ወደ ሌላ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁ፣ የእስራኤልን ከተሞች ሳታዳርሱ የሰው ልጅ ይመጣል።


ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፣ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፣ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፣ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው።


ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፣ “በዐምባው ውስጥ አትቈይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች