የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም በየዋህነት ሄዱ፤ ነገሩንም ሁሉ ከቶ አያውቁም ነበር።
1 ሳሙኤል 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፥ የምታደርገውንም አስታውቅሃለሁ፤ የምነግርህንም ቅባው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሴይን ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፤ ከዚያም የምታደርገውን አሳይሃለሁ፤ የምነግርህንም ሰው ትቀባልኛለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፤ ከዚያም የምታደርገውን አሳይሃለሁ፤ የምነግርህንም ሰው ትቀባልኛለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጣ ጥራው፤ እኔም የምታደርገውን ነገር እነግርሃለሁ፤ እኔ የምነግርህንም ሰው ቀብተህ ታነግሣለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይንም መሥዋዕቱ ጥራው፥ የምታደርገውንም አስታውቅሃለሁ፥ የምነግርህንም ቅባልኝ አለው። |
የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም በየዋህነት ሄዱ፤ ነገሩንም ሁሉ ከቶ አያውቁም ነበር።
በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ቀብተው ያንግሡት፤ መለከትም ነፍታችሁ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ በሉ።
የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ በሳሙኤልም እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን ቀቡት።
አንተም ትናገረዋለህ፤ ቃሌንም በአፉ ታደርገዋለህ፤ እኔ አንደበትህንና አንደበቱን አረታለሁ፤ የምታደርጉትንም አለብማችኋለሁ።
እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ይነግሩሃል” አለው።
እንዲህም አለው፥ “ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም ሀገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ልቅሶአቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕዝቤን ሥቃያቸውን ተመልክችአለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል።”