Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የተ​ጠ​ሩ​ትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም በየ​ዋ​ህ​ነት ሄዱ፤ ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ከቶ አያ​ው​ቁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከኢየሩሳሌምም ሁለት መቶ ሰዎች አቤሴሎም ሄዱ፤ በእንግድነት ተጋብዘው በየዋህነት ከመሄዳቸው በቀር፣ ስለ ጕዳዩ የሚያውቁት አንዳችም ነገር አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌምም ሁለት መቶ ሰዎች አብረውት ሄደው ነበር፤ በእንግድነት ተጋብዘው በቅንነት ከመሄዳቸው በስተቀር፥ ስለጉዳዩ ምንም ነገር አያውቁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በአቤሴሎም ጋባዥነት ከእርሱ ጋር ከኢየሩሳሌም የሄዱ ሁለት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ተከትለውት የሄዱት ስለ ሤራው ምንም ነገር ሳያውቁ በቅንነት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር በየዋህነት ከኢየሩሳሌም ሄዱ፥ የሚሆነውንም ነገር ከቶ አያውቁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 15:11
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ለመ​ብ​ላት ወደ ባማ ኮረ​ብታ ሳይ​ወጣ በከ​ተ​ማው ውስጥ ታገ​ኙ​ታ​ላ​ችሁ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን እርሱ የሚ​ባ​ርክ ስለ​ሆነ እርሱ ሳይ​ወጣ ሕዝቡ ምንም አይ​ቀ​ም​ሱ​ምና፥ ከዚ​ያም በኋላ እን​ግ​ዶች ይበ​ላ​ሉና፤ በዚ​ህም ጊዜ ታገ​ኙ​ታ​ላ​ች​ሁና አሁን ውጡ” አሉ​አ​ቸው።


በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።


የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።


እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች