የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳሙኤል ግን፣ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፣ ‘ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳሙኤል ግን፥ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። ጌታም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ ‘ለጌታ ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳሙኤልም “ይህን ለማድረግ እንዴት ይቻለኛል? ሳኦል ይህን ቢሰማ ይገድለኛል!” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ ‘ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ መጥቻለሁ’ ብለህ ጊደር ይዘህ ሂድ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳሙኤልም፦ እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ። እግዚአብሔርም፦ አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ በል።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 16:2
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “ወንድ ስለ​ማ​ላ​ውቅ ይህ እን​ዴት ይሆ​ን​ል​ኛል?” አለ​ችው።


እሴ​ይ​ንም ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ጥራው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቅ​ሃ​ለሁ፤ የም​ነ​ግ​ር​ህ​ንም ቅባው” አለው።


እር​ሱም፥ “ዘመ​ዶቼ በከ​ተማ ውስጥ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና፥ ወን​ድ​ሞቼም ጠር​ተ​ው​ኛ​ልና እባ​ክህ! አሰ​ና​ብ​ተኝ፤ አሁ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ልሂ​ድና ወን​ድ​ሞ​ቼን ልይ አለ፤ ስለ​ዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አል​መ​ጣም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ቈነ​ጃ​ጅ​ቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊ​ታ​ችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረ​ብታ ላይ መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ አለ​ባ​ቸ​ውና።