የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን እቀ​ባህ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ፤ አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ፣ እግዚአብሔር የላከው እኔን ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አሁን ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እንድቀባህ ጌታ ላከኝ፤ አሁንም የጌታን ቃል ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ እግዚአብሔር የላከኝ እኔ ነኝ፤ አሁንም ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፦ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 15:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ሳ​ዕም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል ይሸ​መ​ታል” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ፈሩ፥ ብታ​መ​ል​ኩ​ትም፥ ቃሉ​ንም ብት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ባታ​ምፁ፥ እና​ን​ተና በእ​ና​ንተ ላይ የነ​ገ​ሠው ንጉሥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ከ​ተሉ፥ መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በድ​ለ​ኻል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛ​ዙን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ን​ቶ​ልህ ነበር።


ገናም ሳኦል ሳይ​መጣ ከአ​ንድ ቀን በፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ጆሮ​ውን ከፈ​ተ​ለት፥


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ነገ በዚ​ህች ሰዓት ከብ​ን​ያም ሀገር አንድ ሰው እል​ክ​ል​ሃ​ለሁ፤ ልቅ​ሶ​አ​ቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕ​ዝ​ቤን ሥቃ​ያ​ቸ​ውን ተመ​ል​ክ​ች​አ​ለ​ሁና ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ሕዝ​ቤን ያድ​ናል።”