የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤ​ልም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አን​ግ​ሼ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ጥያቄአችሁን ሁሉ ተቀብዬ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳሙኤልም እስራኤልን ሁሉ አለ፦ የነገራችሁኝን ሁሉ ሰምቼ አንግሼላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 12:1
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።


አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”