Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ጌል​ገላ ሄዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ቀብቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ አነ​ገ​ሠው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህል ቍር​ባ​ንና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በእግዚአብሔር ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ ታላቅ በዓል አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በጌታ ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ በታላቅ ደስታ አከበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፥ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 11:15
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”


ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እን​ዲ​ሄዱ አዘ​ዛ​ቸው።


አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።


የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።”


ሕዝቡ ግን የሳ​ሙ​ኤ​ልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ጐል​ማ​ሶች ላከ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ችን ሠዉ።


ሳሙ​ኤ​ልም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አን​ግ​ሼ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ንጉ​ሡም ተመ​ልሶ እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ መጣ። የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ንጉ​ሡን ሊቀ​በሉ፥ ንጉ​ሡ​ንም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊያ​ሻ​ግሩ ወደ ጌል​ገላ መጡ።


ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች