የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በባማ ባለው በቤ​ዜ​ቅም ቈጠ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦል ቤዜቅ በተባለ ስፍራ ሰራዊቱን በሰበሰበ ጊዜ፤ ቍጥራቸው ከእስራኤል ሦስት መቶ ሺሕ፣ ከይሁዳም ሠላሳ ሺሕ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል ቤዜቅ በተባለ ስፍራ ሠራዊቱን በሰበሰበ ጊዜ፤ ቁጥራቸው ከእስራኤል ሦስት መቶ ሺህ፥ ከይሁዳም ሠላሳ ሺህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልም ቤዜቅ በተባለ ስፍራ ሰበሰባቸው፤ የቊጥራቸውም ብዛት ከእስራኤል የመጡት ሦስት መቶ ሺህ ሲሆን ከይሁዳ የመጡት ሠላሳ ሺህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በቤዜቅም ቆጠራቸው፥ የእስራኤልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 11:8
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​አ​ብም የሕ​ዝ​ቡን ቍጥር ድምር ለን​ጉሡ ሰጠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይ​ሁ​ዳም ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎች አም​ስት መቶ ሺህ ነበሩ።


በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮ​ራም ከሰ​ማ​ርያ ወጥቶ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ የሕ​ዝቡ ሁሉ አለ​ቆች ሰይፍ በሚ​መ​ዝዙ፥ በቍ​ጥ​ርም አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች በሆኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ጉባኤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።


የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው።


ሳሙ​ኤ​ልም ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሊገ​ናኙ ሄዱ። ከጌ​ል​ጌ​ላም ተነ​ሥ​ተው ወደ ብን​ያም ገባ​ዖን መጡ፤ ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድ​ስት መቶም የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን ጠርቶ በጌ​ል​ጌላ ቈጠ​ራ​ቸው፤ አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች፥ ከይ​ሁ​ዳም ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበሩ።