Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሳሙ​ኤ​ልም ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሊገ​ናኙ ሄዱ። ከጌ​ል​ጌ​ላም ተነ​ሥ​ተው ወደ ብን​ያም ገባ​ዖን መጡ፤ ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድ​ስት መቶም የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያ በኋላ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳኦልም ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ቈጠራቸው፤ ብዛታቸውም ስድስት መቶ ያህል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ሄደ። ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፤ ስድስት መቶ ያህል ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ ሄደ፤ ሳኦልም ከወታደሮቹ ጋር ለመደባለቅ ሲሄድ የቀሩት ሰዎች ተከተሉት፤ ከጌልገላም ተነሥተው በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄዱ፤ ሳኦልም ሠራዊቱን በቈጠረ ጊዜ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልገላም ተነሥተው ወደ ብንያም ጊብዓ መጡ፥ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቆጠረ፥ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:15
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።


ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ።


ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ገ​ና​ኘት በጥ​ዋት ገሥ​ግሦ ሄደ። ለሳ​ሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ መጣ፤ እነ​ሆም፥ ለራሱ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገ​ሩት። ሳሙ​ኤ​ልም ሰረ​ገ​ላ​ውን መልሶ ወደ ጌል​ጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ከአ​መ​ጣ​ውም ከአ​ማ​ረው ከም​ር​ኮው መንጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሲሠዋ አገ​ኘው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች