የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ በሳ​ኦል ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ መጣ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ቁጣውም እጅግ ነደደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልም ይህን በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኀይል ወረደ፤ የሳኦልም ቊጣ እጅግ ገነፈለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህንም ነገር በሰማው ጊዜ በሳኦል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደ፥ ቁጣውም እጅግ ነደደ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 11:6
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው።


ሙሴም በም​ድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የዋህ ሰው ነበረ።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።


ተቈጡ፤ አት​በ​ድ​ሉም፤ ፀሐይ ሳይ​ጠ​ል​ቅም ቍጣ​ች​ሁን አብ​ርዱ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በዮ​ፍ​ታሔ ላይ መጣ፤ እር​ሱም የም​ናሴ ዕጣ ከም​ት​ሆን ከገ​ለ​ዓድ ምድ​ርና ከገ​ለ​ዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻ​ገረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሶ​ራ​ሕና በእ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ የፍ​የል ጠቦ​ትን እን​ደ​ሚ​ጥ​ልም ጣለው፤ በእ​ጁም እንደ ኢም​ንት ሆነ፤ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ አል​ተ​ና​ገ​ረም።


የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች።


ጌዴ​ዎ​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አጸ​ናው፤ እር​ሱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ አብ​ዔ​ዜ​ርም በኋ​ላው ጮኸ።


ወደ​ዚ​ያም ኮረ​ብታ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነ​ቢ​ያት ጉባኤ አገ​ኙት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከሳ​ኦል ራቀ፤ ክፉም መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀው።