የሞትስ ነገር እንዲህ ነው፤ ከልዑል ዘንድ የትእዛዝ ቃል ከመጣ በኋላ፥ እገሌ ይሙት ባለ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ትለያለች፤ ዳግመኛም ወደ ሰጣት ትመለሳለች፤ ለልዑል ጌትነትም አስቀድማ ትሰግዳለች።