ኢያሱ 3:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፥ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፥ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፥ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ። |
የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክና በመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎ ቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለው በቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምን ተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣
ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ።
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን በሙሉ ብርቱ የምሥራቅ ነፋስ አስነሥቶ ባሕሩን ወደ ኋላ በማሸሽ ደረቅ ምድር አደረገው፤ ውሃውም ተከፈለ።
በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ ውሃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይፈስሳል፤ ወደ ባሕሩ ወደሚገባበት ወደ ዓረባ ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ሲፈስስ፣ በዚያ የነበረው ውሃ ንጹሕ ይሆናል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ፣ በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?
“ ‘የደቡብ ድንበራችሁ በኤዶም ወሰን ላይ ካለው ከጺን ምድረ በዳ ጥቂቱን ይጨምራል፤ በምሥራቅም በኩል የደቡብ ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ጫፍ ይጀምርና
ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ዓረባ በተባለው ምድረ በዳ ከሱጵ ትይዩ፣ በፋራንና በጦፌል፣ በላባን፣ በሐጼሮትና በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፣ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።
እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር እስከ ጨው ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤትየሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።
የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ገና እግራቸውን በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ እንዳስገቡ፣ ቍልቍል የሚወርደው ውሃ ወዲያውኑ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”
በዚህ ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ያሉት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፣ በባሕሩም ዳርቻ ያሉ የከነዓናውያን ነገሥታት በሙሉ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን እስክንሻገር ወንዙን በእስራኤላውያን ፊት እንዴት እንዳደረቀው በሰሙ ጊዜ፣ ልባቸው በፍርሀት ቀለጠ፤ እስራኤላውያንንም ለመቋቋም ድፍረት ዐጡ።
የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደ ተሰማም እግዚአብሔር በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሰራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ ወደ ቤትሺጣ፣ ከዚያም ዐልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።