ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፥ ዓሣ አጥማጆች የነበሩትን ሁለት ወንድማማች እነርሱም ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን፥ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ።
ሉቃስ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በባሕሩ ዳር ተጠግተው የቆሙትን ሁለት ጀልባዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረባቸውን ያጥቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕሩ ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕሩም ዳር ሁለት ታንኳዎች ቁመው አየ፤ ከእነርሱም ውስጥ ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን ሊያጥቡ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕር ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ግን ከእነርሱ ውስጥ ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። |
ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፥ ዓሣ አጥማጆች የነበሩትን ሁለት ወንድማማች እነርሱም ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን፥ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ።
ከዚያም እልፍ ብሎ፥ የዘብዴዎስ ልጆች የሆኑትን ሌሎች ሁለት ወንድማማች ያዕቆብንና ዮሐንስን አየ። እነርሱም ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ላይ ሆነው መረባቸውን ሲጠግኑ ሳለ ጠራቸው።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አያቸው።
ከዚያም ጥቂት አለፍ እንዳለ፥ ሌሎች ሁለት ወንድማማችን አየ፤ እነርሱም የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ፤ እነርሱ በጀልባ ላይ ሆነው መረባቸውን ይጠግኑ ነበር፤
ኢየሱስ ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ፥ የስምዖን ወደሆነችው ገባ። ስምዖንንም “ይህችን ጀልባ ከምድር ወደ ባሕሩ እስቲ ጥቂት ፈቀቅ አድርግልኝ” አለው። ከዚህም በኋላ በጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር።