ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤
2 ሳሙኤል 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መገደሉን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በድንጋጤ ተሸበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ደነገጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መሞቱን በሰማ ጊዜ ወኔ ከዳው፤ መላው እስራኤልም ተሸበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆቹም ደከሙ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ደነገጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ እጁ ደከመች፥ እስራኤላውያንም ሁሉ ደነገጡ። |
ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤
አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ነዋሪዎች የሆኑት ሕዝቦች አይሁድን በማስፈራራትና ተስፋ ለማስቈረጥ በመሞከር ቤተ መቅደሱን እንዳይሠሩ ሊከለክሉአቸው ተነሣሡ።