መላው ዓለም በቀሚሱ ላይ ተስሎ ነበር፤ የከበሩ የአባቶች ስሞች በአራቱ ረድፍ ደንጊያዎች፥ ያንተ ግርማም በአክሊሉ ላይ ተቀርጿል።
የዓለሙ ክህነት ሁሉ በልብሱ ጫፍ ላይ ነበርና፥ ባሕርይ በሚባሉ ዕንቍዎች አራት ዙሪያዎች የተቀረጸው የአበውም ክብር በጫንቃው ላይ ነበርና፥ የአንተም ልዕልና በራሱ አክሊል ላይ ነበርና።