ሩፋኤል ልጁን “ወንድሜ ጦብያ” አለው። እርሱም “አቤት” አለው። መልአኩም ቀጠለና “ዛሬ ሌሊት ማደር የሚገባን በዘመድህ በራጉኤል ቤት ነው፥ ሣራ የምትባል ልጅ አለችው፤
ከዘመዶችዋም ወገን አንተ አለህ፤ ልጂቱም ደግና ልባም ናት።