ከቆንጆ ሴት ዓይንህን መልስ፤ የሌላ የሆነውን ውበት አትከጅል። በሴት ቁንጅና ምክንያት ብዙዎች ተሳስተዋል፤ ይህም ስሜትን እንደ እሳት ያቀጣጥላል።
ከመልከ መልካም ሴት ዐይንህን መልስ፤ የሌላ ሚስትም ደም ግባትዋ አያስጐምጅህ፤ በሴት ደም ግባት የሳቱ ሰዎች ብዙዎች ናቸውና፤ ስለዚህ ነገር ፍቅሯ እንደ እሳት ይነድዳል።