በጌጥ የተሠራ የተቀደሰ የወርቅ ልብስ፥ በአዋቂ የተሠራ ወይን ጠጅ ከፋይ፥ ጠቢብ የሠራቸው የተጐነጐኑ የቀያይ የፍርድ ሜዳልያዎች፥
የተለየ ሰማያዊ ሐር ያለበት አራት ኅብርን፥ አምስተኛ ወርቀ ዘቦ ያለበት በነጭ ሐር የተሠራ ልብስንም፥ በሚገባና በእውነት ነገር የተሠራ ልብሰ መትከፍ አለበሰው።