ከያዕቆብ ዘር አንድ ደግ ሰው ፈጠረ፤ እርሱም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አገኘ፤ በእግዚአብሔርና በሰዎች ዘንድ የተወደደው፥ የሙሴ መታሰቢያው የተባረከ ነው።
ሙሴም ስም አጠራሩ የተባረከ ነው፤ መታሰቢያውና አምሳሉም እንደ ቅዱሳን ክብር ነው።