እግዚአብሔርም በዘሩ አማካኝነት ሕዝቦችን ሊባርክ፥ እንደ ምድር ትቢያ ሊያበዛው፥ ዘሮቹን እንደ ከዋክብት ከፍ ከፍ ሊያደርግ፥ ምድርን ሊሰጣቸው፥ ከአንዱ ባሕር ወደ ሌላው፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻዎች ሊያወርሳቸው ማለለት።
ስለዚህም አሕዛብ በዘሩ ይባረኩ ዘንድ፥ እንደ ባሕር አሸዋም ያበዛቸው ዘንድ፥ ዘሩም እንደ ሰማይ ከዋክብት ይበዙ ዘንድ፥ ከባሕር እስከ ባሕርም ድረስ ያወርሳቸው ዘንድ፥ ከወንዞችም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያወርሳቸው ዘንድ ቃል ኪዳንን አጸናለት፥