ንጋት ላይ በንጹሕ ልቡ ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሔር ፊቱን ይመልሳል፤ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ልመናውን ያቀርባል፥ አፉንም የሚያሟሸው በጸሎት ነው፥ ስለ ኃጢአቱም ይቅርታን ይለምናል።
ሰዎችን በበጎም፥ በክፉም ትፈትናቸዋለችና፥ ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሔር ይሄድ ዘንድ፥ በልዑልም ፊት ይጸልይ ዘንድ ልቡን ይመልሳል፤ አፉንም ይከፍታል፤ ይለምናልም፤ ስለ ኀጢአቱም ይናዘዛል።