መዝሙር 96:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስክና በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ፥ የዱር ዛፎችም ሁሉ በጌታ ፊት ደስ ይበላቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማሳና በላይዋ የሚገኙ ሰብሎች ሁሉ ደስ ይበላቸው! ከዚያም የደን ዛፎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደስታ ይዘምሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይላቸዋል። ለቅድስናውም መታሰቢያ ያመሰግናሉ። |
እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።