ጌታ ባይረዳኝ ኖሮ ነፍሴ ወዲያው ሲኦል በወረደች ነበር።
እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣ ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።
እግዚአብሔር ባይረዳኝ ኖሮ፥ ፈጥኜ ወደ ሙታን ዓለም በወረድኩ ነበር።
አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፥
ገፈተሩኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፥ ጌታ ግን አገዘኝ።
የዕርገት መዝሙር። በጌታ የታመኑ እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?
ፊትህን በባርያህ ላይ አብራ፥ ስለ ምሕረትህም አድነኝ።
እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።