መዝሙር 80:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንባ እንጀራን መገብካቸው፥ እንባም በስፍር አጠጣሃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያችን ያሉ መንግሥታት መሬታችንን ለመውሰድ እርስ በእርሳቸው እንዲዋጉ አደረግህ፤ ጠላቶቻችን ሁሉ ይሳለቁብናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጀርባውን ከመስገጃቸው መለሰ፥ እጆቹም በቅርጫት ተገዙ። |
የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
ስለዚህ፥ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆዎች፥ ለፈራረሱ ቦታዎችና ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት ሕዝቦች ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፥
እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ዕጣ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።
እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፥ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሶሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፥