መዝሙር 73:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሹፈት ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤ በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓላት ከምድር እንሻር |
ከንቱ ወደ ሆነው ነገር ተመለሱ፤ እንደ ረገበ ቀስት ሆኑ፤ አለቆቻቸው ከክፉ አንደበታቸው የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህ በግብጽ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤
በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው።