አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥ በኃይልህም ፍረድልኝ።
ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤ እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ
ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤ ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።
ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥ ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
ሁልጊዜ ጌታን በፊቴ አየዋለሁ፥ በቀኜ ነውና አልታወክም።
በመከራ ቀን ጌታ ይስማህ፥ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወረድኸኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።
ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥ አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥ እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና።
አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥ ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም።
ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።