መዝሙር 50:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤ የሚባላ እሳት በፊቱ፣ የሚያስፈራ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በደሌን አውቃለሁና፥ ኀጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። |
እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስ መጣ፥ በዙሪያው ብርሃን ያለው መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበር፥ በእሳቱም መካከል የሚያንጸባርቅ ነገር ነበረ።
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።
እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ ዛሬ የሚያልፈው ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን እወቅ፥ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ ጌታ ተስፋ እንደሰጠህ አንተም ታሳድዳቸዋለህ፥ በፍጥነትም ታጠፋቸዋለህ።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።