Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 48:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤ እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤ አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤ ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 48:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።


በአንተ ምክር መራኸኝ፥ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።


የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።


ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥ ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።


ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥ እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።


የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፥ በዙሪያው ፍርሃት ነበረ፥ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ።


ጌታን፦ “አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ”፥ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።


እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድም ጎዳና መካከል፥


ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ።


ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።


ሕዝብህን እስራኤልን ለዘለዓለም ያንተው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጽንተኸዋል፤ ጌታ ሆይ፤ አንተም አምላክ ሆነኸዋል።


እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች